fbpx
Connect with us

እንተዋወቅ

ዶክተር ተመስገን እንዳለዉ እባላለሁ። በሙያዬ በህክምና እና ትምህርት ቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ የተሰማራሁ ስሆን፣ አብዛኞቹን የእድሜዬን ቀናቶች በትምህርት እና ንባብ ላይ አሳልፍያለሁ። በመጀመሪያ የአገሬ ወጣቶች በቀላሉ በመረጃ መረብ ላይ የተለያዩ ሙያዎችን በአጭር ጊዜ መማር የሚችሉ ቢሆንም አብዛኞቹ ጦማሮች የተዘጋጁት በአማርኛ ስላልሆነ እና ይሄም የቋንቋ ችግር ያሰቡትን እንዳያደርጉ ተስፋ ሲያስቆርጣቸዉ በሰፊዉ ይስተዋላል። በመሆኑም ይሄንን ችግር ለመቅረፍ የተለያዩ አጫጭር ጦማሮችን በአማርኛ በማዘጋጀት የበኩሌን ለማበርከት የታሰበ ድረ ገጽ ነዉ። በመቀጠልም በየጊዜዉ ጥናቶች ላይ የተመሰረተ እና ህብረተሰቡን ያሳተፈ የጤና መረጃ ስርጭትም አናሳ በመሆኑ፡ የተለያዩ በህብረተሰባችን ላይ ጎልቶ በሚታዩ የጤና እክሎች ላይ አጫጭር ትምህርቶችን በማዘጋጀት እና ከህብረተሰቡም ለሚነሱ ጥያቄዎች በጥናቶች የተደገፈ ምላሽ ለመስጠት የታሰበም ጭምር ነዉ። ከነዚህ ዋና ዋና  ሃሳቦች በመነሳት በጤና፣ ቴክኖሎጂ እና ትምህርት ላይ ያተኮሩ ትምህርቶችን በየእለቱ በማዘጋጀት ህብረተሰቡን ለመድረስ የተዘጋጀ ጦማር ነዉ።

✍️ አላማዉ፡-
👉 ኢትዮጵያዉያን ወጣቶች አቅማቸዉን እንዲጠቀሙ ማስቻል፣
👉 የተሻለ የጤና አገልግሎት እና ትምህርት ቴክኖሎጂ ተደራሽ ማድረግ፣
👉 የወደፊቱን የቴክኖሎጂ እድገቶች ለወጣቶች ማስተዋወቅ፣

✍️ ግብ፡-
👉በየዕለቱ የተለያዩ የሚያንጹ እና የሚያስተምሩ ጦማሮችን በማዘጋጀት ለሀገሬ ወጣቶች በማድረስ በሚቀጥሉት 5 ዓመታት ከ100, 000 የሚበልጡ የሀገሬን ወጣቶች በተገቢዉ ክህሎት እና እዉቀት መግራት፣
👉 በርቀት ህክምና በመጠቀም ለህዝቦች ጤና ዕክል መፍትሄ መስጠት።

✍️ ይሄንን አላማ ለመደገፍ ወይም አብራችሁኝ ለመስራት የምትፈልጉ በሚከተሉት አድራሻዎች ልታገኙኝ ትችላላችሁ።
👉 የግል Website እና ጦማር ፡- https://drtemesgen.com/
👉 የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/doctortemesgen
👉 የTwitter ገጽ፡- https://twitter.com/doctortemesgen
👉 የInstagram ገጽ፡- https://twitter.com/doctortemesgen
👉 የ Linkedin ገጽ፡- Linkedin ላይ መልዕክት ይላኩልኝ
👉 የ You tube ቻናል፡- ቪድዮዎችን በዩትዩብ ይመልከቱ
👉 ስልክ ቁጥር፡- +251-916-186-507አመሰግናለሁ።
ዶክተር ተመስገን እንዳለዉ
በቅዱስ ጳዉሉስ ሆስፒታል ሌክቸረር፣ UX & UI Developer, Blogger, Mentor and Consultant Social Media Manager.
ሌሎች መተግበሪያዎች ላይ ሳይሄዱ በአጭሩ መልክት እንዲደርሰኝ ከስር ባለዉ ቀጽ ይላኩልኝ።

References:-
1. Arbaminch University Website

 

To Top