fbpx
Connect with us

ፌስቡክ በናይጄሪያ ቢሮዉን ሊከፍት ነዉ።

Social Media

ሳይቴክ

ፌስቡክ በናይጄሪያ ቢሮዉን ሊከፍት ነዉ።

የማህበራዊ ድረ ገጹ ባለ ትልቁ ድርሻ የሆነዉ የአሜሪካዉ ቴክኖሎጂ ኩባንያ ፌስቡክ በአፍሪካ አህጉር ሁለተኛ የሆነዉን ቢሮ በናይጄሪያ ሊከፍት እንደሆነ አሳውቋል። ከ 5 ዓመታት በፊት በአፍሪካ አህጉር የመጀመሪያ የሆነዉን ቢሮ በደቡብ አፍሪካ የከፈተዉ ፌስቡክ አሁን ደግሞ በናይጄሪያ ሌጎስ ከተማ ሁለተኛ ቢሮ በመክፈት አፍሪካዉያኑን ለማገልገል ወጥኗል።

እንደ ኩባንያዉ ገለጻ በናይጄሪያ የሚከፈተዉ ቢሮ በቴክኖሎጂዋ ዋና ከተማ ሌጎስ እንደሚሆንና ስራዉን እንደጎርጎሮሳዉያኑ 2021 ዓመት ሁለተኛ መንፈቅ እንደሚጀምርም ገልጿል። ይህም የሚከፈተዉ ቢሮ የታችኛዉ ሰሃራ አፍሪካ ሀገራትን በእጅጉ የሚያግዝ እንደሆነም አሳውቋል።

ለፌስቡክ አፍሪካ ሬጅናል ዳይሬክተር የሆነችዉ Nunu Ntshingla እንዳለች፡- ሁለተኛ ቢሯችንን በአፍሪካ ሀገር በሆነችዉ ናይጄሪያ በመክፈታችን ተደስተናል። በደቡብ አፍሪካዋ ጆሃንበርግ ከተማ ከከፈትነዉ የመጀመሪያ የአፍሪካ ቢሮ በኋላ በናይጄሪያ የምንከፍተዉም ቢሮ እንደ ደቡብ አፍሪካዉ ቢሮ የተለያዩ ተሰጥኦ ያላቸዉን አፍሪካዉያን ለማገዝ እና አገልግሎቶቻችንን ለአዳዲስ ደምበኞች ለማስፋትም ይዉላል ስትል ተናግራለች።በናይጄሪያ የሚከፈተዉም ቢሮ በአፍሪካ የመጀመሪያዉ እና ኤክስፐርት እንጂነሮችን የያዘ ቡድን በንግድ፣ ግኑኝነት እና ትብብር ላይ በማትኮር የወደፊቱን የአፍሪካ ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት እንደሚገነቡም ጠቁመዋል።

በእቅዱም ላይ የኩባንያዉ አዲስ ምርት ሙከራ አስተባባሪ Ime Archibong እንደገለጸዉ በናይጄሪያ ሌጎስ ከተማ የሚከፈተዉ ቢሮ ለአጉሪቱ በድጂታል ቴክኖሎጂዉ መስክ አዳዲስ የፈጠራ እድል የሚከፍት እና ምርቶችን ከአፍሪካ ለአለም የሚያስተዋውቅም እንደሆነ ገልጸዋል። በአፍሪካ የቴክኖሎጂ ስርዓት ከፍተኛ የፈጠራ አቅም ያለ በመሆኑ ያንን ተጠቀመዉ ለአፍሪካ የወደፊት ቴክኖሎጂ መሠረት እና ለአለምም የሚሆኑ ምርቶችን ለማሳካትም እንዳሰቡ ጨምሮ ጠቅሷል።

በአለማችን ላይ ከ 70 ከተሞች በላይ ቢሮዎች ያሉት ፌስቡክ ኩባንያ 17 የዳታ ማዕከሎች እና ከ 52,000 በላይ ቋሚ ሰራተኞች ያሉት ሲሆን ከተለያዩ ትላልቅ የቴሌኮም ድርጅቶች ጋር በመሆን የአለማችንን ትልቁን የባህር ላይ የእንተርኔት መስመር በመዘርጋት በአፍሪካ አህጉር ፈጣን ኢንተርኔት መስመር እያዘጉ እንደሆነ ጨምሮ ገልጿል።

ምንጭ፡- ቢቢሲ

Continue Reading
You may also like...

MD, Lecturer, UX & UI Developer, Consultant SMM, and Blogger.

Click to comment

More in ሳይቴክ

To Top