fbpx
Connect with us

እምነትም ከመስማት ነዉና… የእንቁራሪቱ ታሪክ

Pixabay

ካነበብኳቸዉ

እምነትም ከመስማት ነዉና… የእንቁራሪቱ ታሪክ

በአንድ ጊዜ እንቁራሪቶች ሰብሰብ ብለዉ በጫካ ዉስጥ እየተጓዙ፣ ከመሃላቸዉ ሁለቱ ሳያዩ መዉጣት ወደሚከብድ ጉድጓድ ዉስጥ ይወድቃሉ። የወደቁትም ከጉድጓዱ ለመዉጣት እየተፍጨረጨሩ መዝለል ጀመሩ።

ሌሎችም ወደ ኋላ ተመልሰዉ ወደ ጉድጓዱ ዝቅ ብለዉ እያዩ በጣም ጥልቅ ነዉ፣ መቼም ሊወጡ አይችሉም፣ እያሉ መነጋገር ጀመሩ። ዝናብም መጣል እየጀመረ ነበርና አንዳቸዉ ጉድጓዱ በዝናብ ዉሃ ስለሚሞላ ተዋኝተዉ ሊወጡ ይችላሉ ሲል ተናገረ።

ነገር ግን ሁለቱም ለመዉጣት እየተፍጨረጨሩ መዝለሉን ቀጠሉ። ከጉድጓዱ ዉጭ ያሉቱ፣ ተዉ እትልፉ፣ ጉልበት አትጨርሱ፣ አይሳካላችሁም… ነገር ግን ዝናብ እየዘነበ ስለሆነ ጉድጓዱ በዉሃ ስለሚሞላ ተዋኝታችሁ ትወጣላችሁ እያሉ ተናገሯቸዉ።

አንደኛዉም የነሱን ንግግር ሰምቶ ተስፋ በመቁረጥ መሞከር አቆመ። ሁለተኛዉ ግን ሙከራዉን ቀጠለ። ከዉጭ ያሉትም ጉልበትህን አትጨርስ… እኛ ያቀድነቀዉ እቅድ አለ። በራስህ አትሞክር፣ ባትደክም ነዉ የሚሻልህ እያሉ ቢጎተጉቱትም እርሱ ግን ሙከራዉን አላቆመም ነበር።

እርሱ ግን የሚሉትን እየሰማ ስላልነበረ መጨረሻ ላይም ተሳክቶለት በመዝለል ወጣ። ከዚያም ሁሉም በመገረም ኢያዩት…
እሱም ወደነሱ በመዞር… ስላበረታታችሁኝ አመሰግናለሁ አላቸዉ እጃቸዉን ሲያወራጩ ስለነበር ስላየ። እነሱ ግን በመገረም… የምን ማበረታታት… እየሰማን አልነበርም ማለት ነዉ?! በማለት ጆሮዉ መስማት እንደማይችል ገባቸዉ።

ከዚያም ወደ ጉድጓዱ በመመለስ ለሌላኛዉም ተነስ፣ ትችላለህ፣ዝለል፣ ዝለል፣ ዝለል እያሉ ማበረታት ጀመሩ። ሌላኛዉም ተስፋ ቆርጦ የቀረዉም ከጉድጓዱ በመዝለል ሊወጣ ቻለ ይባላል።

ከዚህ ታሪክ የምንማረዉ፡-
1ኛ. የሆነን ነገር ላይ ያለን እምነት የሚገነባዉ አካባቢያችን ላይ ባሉ ሰዎች እምነት፣ ንግግር፣ በምናነባቸዉ ወይም ወደ ዉስጣችን እንዲገቡ በፈቀድንላቸዉ መረጃዎች ላይ ስለሆነ፤ ምን እንድንበላ እንደምንጠነቀዉ ሁሉ ምን እንደምንሰማ እና እንደምናይ መጠንቀቅ አለብን። ምክንያቱም እምነት ከመስማት ነዉና…። አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ሳያውቁ በየዋህነት ወይም ደግሞ ከፊትህ ያለዉን ድል በማየት እንዳይሳካላህ በቅናት የተለያዩ ነገሮችን በመናገር ተስፋ እንድትቆርጥ ሊያደርጉህ ይሞክሩ ይሆናል። ስለአንተ ማንነት ወይም አቅም ሌሎች ክፉ እንዲነግሩህና እና ተስፋ እንዲያስቆርጡህ አትፍቀድ።
2ኛ. አንድ ሰዉ የሆነን ነገር ለማሳካት የሚያስፈልገዉ ነገር ድንገት ትንሽ ተስፋ ሊሰጠዉ የሚችል ድምጽ ብቻ ሊሆን ስለሚችል ከአፍህ የሚወጣዉን ነገር በደንምብ ብታስተዉለዉ መልካም ነዉ እላለሁ።
አመሰግናለሁ።

MD, Lecturer, UX & UI Developer, Consultant SMM, and Blogger.

Click to comment

More in ካነበብኳቸዉ

To Top