fbpx
Connect with us

ለ ታይሮቶክሲሰኮሲስ ህክምና የ PTU አማራጭ መድሃኒት…?

PTU alternative
Social Media

ህክምና

ለ ታይሮቶክሲሰኮሲስ ህክምና የ PTU አማራጭ መድሃኒት…?

የቴሌ ህክምና ታካሚ ጥያቄ፡- ታይሮቶክሲኮሲስ የሚባል ህመም አለብህ ተብዬ PTU የሚባል መድሃኒት እወስድ ነበር ነገር ግን አሁን ላይ በገበያ ላይ የለም እየተባልኩ ለእንድ ወር ለሚሆነኝ መድሃኒት በፊት ስገዛ ከነበረዉ ዋጋ በብዙ እጥፍ በመሆኑ መድሃኒቱን ላቋርጥ ተገደድኩ። ከ PTU ዉጭ ሌላ አማራጭ መድሃኒት አለ ወይ?

ታይሮቶክሲኮሲስ ማለት የታይሮይድ እጢ ከልክ በላይ ታይሮይድ ሆርሞን በሚያመነጭበት ጊዜ ከልክ በላይ የሚመረተዉ ሆርሞንም በሰዉነታችን ላይ የተለያዩ ጫናዎችን በማሳደር ጤናችን እንዲዛባ በማድረጉ የሚመጣ ህመም ነዉ። ስለዚህ ይሄንን የሆርሞን መመረት ለመቀነስ ከሚደረጉ ህክምናዎች መካከል፡- የመድሃኒት ህክምና፣ የጨረራማ አዮዲን ህክምና እና ቀዶ ህክምና እንደ አማራጭ ይቀርባሉ።
ከመድሃኒቶቹ መካከል አንዱ እና በሃገራችን በብዛት የተለመደዉ PTU ፕሮፓይል ታዮ ዩራሲል የተሰኘዉ ሲሆን ሌሎች እኛ ሀገር ሊኖሩ የሚችሉትን እና ከ PTU አንታጻር ያላቸዉን ሁኔታ እንያቸዉ።

ከ PTU ዉጭ ያሉትን መድሃኒቶች ስናይ Carbimazole ወይም Methimazole ከተሰኙት አንዱን መርጦ መጠቀም ይቻላል።
1. PTU ወይም (Propylythiouracil) ፕሮፓይል ታዮ ዩራሲል የሚባለዉ መድሃኒት የሚሰራበት መንገድ የታይሮይድ ሆርሞን የሚመረትበትን መንገድ በማደናቀፍ እና የታይሮይድ ሆርሞን ሰዉነታችን ዉስጥ በመሰራጨት ስራ ወደሚሰራበት አይነት እንዳይቀየር በማድረግ ሲሆን
2. ሌላኛዎቹ ግን ካርቢማዞል (Carbimazole) እና ሜቲማዞል (Methimazole) የተሰኙት ደግሞ የሚሰሩበት መንገድ ታይሮይድ ሆርሞን እንዳይመረት በማደናቀፍ ነዉ።

ከሁለቱም መድሃኒቶች በመጀመሪያ ደረጃነት የሚመረጠዉ Carbimazole የተሰኘዉ ሲሆን፣ PTU ግን በእርግዝና ላይ ላሉ ሴቶች እና ሁለቱንም የሆርሞን መስሪያ መንገዶች በፍጥነት ማለትም የተመረተዉንም ታይሮይድ ሆርሞን ጭምር ስራ እንዳይሰራ እና በጥቂት ቀናት ዉስጥ ለዉጥ ማየት ስንፈለግ እና ታማሚዎቹ Carbimazole እየወሰዱ ካልተስማማቸዉ እና የጎንዮሽ ጉዳቱ ከከበደ PTU ን ልንመርጠዉ እንችላለን።
ከሁለቱም መድሃኒቶች የጎንዮሽ ጉዳት ብናይ ቀለል ያለ የጎንዮሽ ጉዳት ያለዉ Carbimazole ነዉ።
አሁን ላይ ሰሞኑን ገበያ ላይ ባለዉ ዋጋ ስናይ የ Carbimazole ዋጋ ቀለል ስለሚል እሱን መጠቀም ይቻላል።  ካርቢማዞል አወሳሰድ መጠኑ አሁን ላይ ባለዉ የ ታይሮይድ ሆርሞን ምርት ላይ መሰረት ያደረገ ሲሆን ይሄንን ከሚከታተልዎ ሃኪም ጋር በመመካከር የመድሃኒቱን መጠን ማስተካከል ይቻላል።
በተቻለ መጠን መድሃኒቶቹ ሲወሰዱ አንዴ ታዟል በማለት የሃኪም ክትትል ማቋረጥ ተገቢ አይደለም። ለምሳሌ ቢያንስ በየ ሁለት ወር ወይም በ 3 ወር አንዴ የሆርሞኖቹን መጠን እና ሌሎችንም መድሃኒቱን ከመዉሰድ ጋር ሊገናኙ የሚችሉ የጎንዮሽ ጉዳቶችንም ሆነ የህክምናዉን ዉጤታማነት መከታተል ያስፈልጋል። መድሃኒቱም ቢሆን መቆም ሊኖርበት የሚችልበት ሁኔታ ስለሚኖር ክትትል ያለማቆሙ መልካም ነዉ።

አመሰግናለሁ።
ዶ/ር ተመስገን እንዳለዉ።

MD, Lecturer, UX & UI Developer, Consultant SMM, and Blogger.

2 Comments

More in ህክምና

To Top