fbpx
Connect with us

የስኳር ህመም ሰዉነታችንን እንዴት ይጎዳዋል?

featured
Pixabay

ህክምና

የስኳር ህመም ሰዉነታችንን እንዴት ይጎዳዋል?

በአለማችን ላይ ወደ 422 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ከስኳር ህመም ጋር ይኖራሉ ፡፡ እንደ ጎርጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር በ 2016 ብቻ ወደ 1.6 ሚሊዮን ገደማ ሰዎች በስኳር ህመም ምክንያት ሞተዋል ፡፡ ከጥንት ጊዜያት ጀምሮ የስኳር ህመም በሰው ልጆች ላይ ተጽዕኖ ሲያሳድር ኖሯል ፡፡ የስኳር ህመም የሚያስከትላቸዉን ጉዳቶች በማወቅ፣ በአግባቡ በመቆጣጠር እና ክትትል በማድረግ ብዙ ሰዎች ረጅም ጤናማ ዕድሜ መኖር ይቻላል፡፡
የስኳር ህመም በደም ውስጥ ያለው የስኳር መጠን በጣም ከፍ በሚልበት ጊዜ እና በተፈጥሮው ሊስተካከል በማይችልበት ሁኔታን የሚፈጥር ሥር የሚሰድ ህመም ነው ፡፡ ሰውነታችን ግሉኮስ ተብሎ የሚጠራውን ስኳር እንደ ዋና የኃይል ምንጭ ይጠቀማል ፣ ነገር ግን ይሄንን ግሉኮስ ለመጠቀም ወደ ሰዉነት ሴሎች (ህዋሳት) ውስጥ መግባት ይኖርበታል ፡፡ ይህ ህዋሳትን (ሴሎችን) ስኳር እንዲቀበሉ ምልክት የሚሰጠዉ ሆርሞን ኢንሱሊን በሚባል ይታወቃል ፡፡

የስኳር ህመም የሚከሰተዉ ደግሞ ይሄ ግሉኮስ ወደ ህዋሳት ውስጥ እንዲገባ እና ጥቅም ላይ እንዲዉል የሚያደርገዉን ኢንሱሊን የሚያመርቱ ህዋሳት ሲሞቱ፣ የሚመረተዉ ኢንሱሊን መጠን ሲያንስ ወይም ትክክለኛ ሳይሆን ሲቀር ወይም ደግሞ የሰዉነታችን ህዋሳት ለኢንሱሊን ሆርሞን ያለመታዘዝ ምክንያት ነዉ።
ይህ ኢንሱሊን የተባለዉ ሆርሞን በሰዉነታችን ቆሽት በሚባለዉ አካል ዉስጥ በሚገኙ ቤታ በሚባሉ የቆሽት ሴሎች ይመረታል። ከተመረተ በኋላም የስኳር መጠን በደም ዉስጥ ከፍ በሚልበት ጊዜ ከቆሽት ሴሎች ይለቀቃል። በደም ዉስጥ የሚገኘዉን የስኳር መጠን የተስተካከለ እንዲሆን በሰዉነታችን ህዋሳት፣ በቆሽት እና በተለያዩ ሆርሞኖች መካከል እጅግ ጤናማ የሆነ መስተጋብር ያስፈልጋል። በዚህ መስተጋብ ላይ የሚገጥሙ ማንኛዉም እክሎች የስኳር ህመምን ሊያስከስቱ ይችላሉ።
ከፍተኛ የሆነ በደም ዉስጥ የሚዘዋወር የስኳር መጠን ከጊዜያት በኋላ ከፍተኛ ጉዳት በሰዉነት ላይ ሊያደርስ ይችላል። ይሄም ጉዳት በተለያዩ የሰዉነት ክፍሎቻችን ባጠቃላይ በትላልቅ እና ጥቃቅን የደም ስሮቻችን ላይ ጉዳት በማድረስ ከጥቅም ዉጭ ሊያደርጋቸዉ ይችላል።

 በትላልቅ የደም ስሮቻችን (Macrovasculature) ላይ ጉዳት ሲያደርስ የልብ ድካም ወይም ድንገትኛ የልብ ጥቃት፣ በአንጎል ላይ እንደ ስትሮክ እና በ እጅና እግራችን ላይ ደግሞ በደም ስሮቹ ከጥቅም ዉጭ በመሆናቸዉ ምክንያት ሊሞቱ ወይም ወደ ጋንግሪን ሊደርሱ ይችላሉ።
በጥቃቅን ደም ስሮች (Microvasculature) ላይ ጉዳት ሲደርስ ደግሞ የአይን መታወር፣ የተለያዩ የሰዉነት ክፍሎቻችን ነርሾች ከጥቅም ዉጭ መሆን እና የኩላሊታችን ከጥቅም ዉጭ የመሆን ወይም መድከም ይገኙበታል።
ይሄንን ጉዳት በተቻለ መጠን ለመቀነስ አስፈላጊዉን ህክምና እና ክትትል ማድረግ ተገቢ ነዉ።
ለሌሎችም ያጋሩ።
አመሰግናለሁ!

MD, Lecturer, UX & UI Developer, Consultant SMM, and Blogger.

2 Comments

More in ህክምና

To Top