fbpx
Connect with us

የስኳር ህመም አይነቶች

featured image
Pixabay

ህክምና

የስኳር ህመም አይነቶች

የስኳር ህመም በደም ውስጥ ያለው የስኳር መጠን በጣም ከፍ በሚልበት ጊዜ የሚፈጥር ሥር የሚሰድ ህመም ሲሆን የሚከሰትበትም ምክንያት ኢንሱሊን የሚያመርቱ ህዋሳት ሲሞቱ፣ የሚመረተዉ ኢንሱሊን መጠን ሲያንስ ወይም ትክክለኛ ሳይሆን ሲቀር እና/ወይም የሰዉነታችን ህዋሳት ለኢንሱሊን ሆርሞን ያለመታዘዝ ምክንያት ነዉ።

የስኳር ህመም ኢንሱሊን የሚያስፈልገዉ እና የማያስፈልገዉ ተብለዉ ሲከፈል የነበረዉ በፊት የነበረዉ እና አሁን የቀረዉ መለያ ሲሆን የቀረበትም ምክንያት ሁሉም አይነት የስኳር ህመሞች እንዳስፈላጊነቱ ተጨማሪ ኢንሱሊን መስጠት ሊኖርብን የሚያስገድድ ደረጃ ሊኖርባቸዉ ስለሚችል ነዉ።
አሁን አገልግሎት ላይ ባለዉ መለያ የስኳር ህመም ባጠቃለይ በሶስት ይከፈላል።
1. የመጀመሪያዉ አይነት የስኳር ህመም
2. ሁለተኛዉ አይነት የስኳር ህመም እና
3. በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት ተብለዉ በሶስት ይከፈላሉ

በመጀመሪያዉ አይነት የስኳር ህመም በዋናነት የሚከሰተዉ የሰዉነታችን የበሽታ መከላከያ ስርዓት ኢንሱሊን ሆርሞንን የሚያመርቱ በቆሽት ዉስጥ የሚገኙ ቤታ የተሰኙትን ህዋሳት ከተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ በስህተት በማጥቃት ሲገላቸዉ እና ሰዉነታችን የኢንሱሊን ሆርሞን ሲያጥርበት የሚከሰት ነዉ። ይሄኛዉም የስኳር ህመም አይነት ከሁሉም አይነቶች እስከ 10 በመቶ የሚደርሱ ታማሚዎች ላይ የሚገኝ ነዉ። ይሄኛዉ አይነት የስኳር ህመም ብዙ ጊዜ በወጣትነት የሚታወቅ እና በዘር እንደሚተላለፍ ጥናቶች ያመለክታሉ።

ሁለተኛዉ አይነት የስኳር ህመም የሚከሰተዉ ደግሞ በሰዉነት ዉስጥ የተመረተዉ ኢንሱሊን ሆርሞን በመጠን ወይም በዉጤታማነት እክል ሲኖርበት አለበለዚያ የተለያዩ የሰዉነት ህዋሳት ለኢንሱሊን ሆርሞን ተገቢ ምላሽ ባለመስጠት የሚከሰተዉ ነዉ። ይሄኛዉም አይነት የስኳር ህመም ከ 80 እስከ 90 በመቶ የሚደርሱ የስኳር ታማሚዎች ላይ የሚገኝ ነዉ። የሰዉነት ህዋሳት ለኢንሱሊን ሆርሞን ተገቢ ምላሽ በመስጠት ግሉኮስ ከደም ወደ ዉስጣቸዉ የማያስገቡበት ምክንያት በግልጽ ባይታወቅም የተወሰኑ አጋላጭ ምክንያቶች ተቀምጠዉለታል። እነርሱም ከመጠን በላይ የሆነ የሰዉነት ዉፍረት፣ እንቅስቃሴ ያለማድረግ፣ ከመጠን ያለፈ እና ስር የሰደደ ዉጥረት እና ተፈጥሮአዊ ይዘታቸዉን የለቀቁ እና ከፍተኛ ካሎሪ የያዙ ምግቦችን ማዘዉተር ይገኙበታል።

ሶስተኛዉ አይነት የስኳር ህመም በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት የስኳር ህመም በመባል የሚታወቅ ነዉ። ይሄኛዉም የስኳር የሚከሰተዉ እናቲቱ ከሷ በተጨማሪ ለሌላ በዉስጧ ለለተፈጠረዉ አካል ተጨማሪ ኢንሱሊን ማምረት ሲኖርባት በሚከሰት ተጽእኖ የሚከሰት ነዉ። ይሄኛዉም የስኳር ህመም አይነት እንዲከሰት ከሚያደርጉ አጋላጭ ምክንያቶች መካከል ከጽንሱ መፈጠር ጋር የተያያዙ የተለያዩ በእናቲቱ ሰዉነት የሚከሰቱ ሆርሞኖች እና በጽንሱ እንግዴ ልጅ የሚመረቱ ሆርሞኖች ጫና ይገኙበታል።
ለጥያቄ ወይም ለማማከር ከድረገጹ ስር በሚገኙ መተግበሪያዎች አንዱን በመጠቀም ያግኙኝ።
አመሰግናለሁ።

MD, Lecturer, UX & UI Developer, Consultant SMM, and Blogger.

Click to comment

More in ህክምና

To Top