fbpx
Connect with us

ባሉበት ሆነዉ ሊሰሩ የሚችሏቸዉ Save the Children ክፍት የስራ ቦታዎች

featured

ጉርሻ

ባሉበት ሆነዉ ሊሰሩ የሚችሏቸዉ Save the Children ክፍት የስራ ቦታዎች

ከኮሮና ወረርሽኝ በኋላ ብዙ ድርጅቶች ስራቸዉን በአብዛኛዉ በድረ ገጽ መተግበር ከጀመሩ ሰነባብተዋል። ይህ ደግሞ ብዙ ስራዎችን መስራት አቅም ያላቸዉን ሰዎች ካሉበት ቦታ ሆነዉ ስራቸዉን መከወን የሚችሉበትን አቅም መፍጠሩ ተመራጭ ያደርገዋል።
ከነዚህ ድርጅቶች መካከል አንዱ እና ብዙ ክፍት የስራ ማስታወቂያዎችን ያወጣዉ Save the Children የተሰኘዉ ግብረ ሰናይ ድርጅት ነዉ። ስለ ድርጅቱ እና ማስታወቂያዎች በዚህ ጽሁፍ ላይ ያገኛሉ።
Save The Children እያንዳንዱ ህጻን እኩል መብቶች እንዲኖሩት ባለፉት 100 ዓመታት በዓለም ላይ በጣም ተጋላጭ የሆኑ ሕፃናት እንዲድኑ ፣ እንዲማሩ እና ጥበቃ እንዲደረግላቸው የሚረዳ ድርጅት ነዉ ፡፡ በየአመቱ ከ 117 በላይ በሚሆኑ ሀገሮች ውስጥ በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሕፃናትን በስራችዉ ያገኛሉ ፡፡ አሁን ደግሞ ለቀጣዩ ስራዎቻቸዉ የሚያግዟቸዉን ባለሙያዎች በአለም ዙሪያ ለመቅጠር እጅግ ብዙ ማስታወቂያዎች አዉጥተዋል። ከነዚህ የስራ ማስታወቂያዎች አብዛኞቹ ከቤታችሁ ሆናችሁ ልትሰሩ የሚያስችሉ ሲሆን ሌላም ስራ እየሰራችሁ ለድርጅቱ ካላችሁበት ቦታ ሆናችሁ መስራት እንድትችሉ እድል ይፈጥራሉ።
አብዛኞቹ ስራዎች ካላችሁበት ቦታ ሆናችሁ መስራት የምትችሉባቸዉ ከመሆናቸዉም በላይ ክፍያቸዉም እጅግ ያማረ ነዉ። ቢያንስ ከ 40,000 ፓዉንድ ጀምሮ ይከፍላሉ።
በነዚህ ስራዎች ላይ እንዲከፈላችሁ የምትፈልጉትን ደሞዝ ጭምር እንድትወስኑ ልትጠየቁ ትችላላችሁ። ከችሎታችሁ እና አገልግሎት ዘመናችሁ አንጻር የምትፈልጉትን ክፍያ መጠየቅም መብታችሁ የተጠበቀ ነዉ።
ለማመልከት የሚያስፈልጋችሁ ነገሮች፡-
1. በተመዘገባቸሁት የማመልከቻ አካዉንት ላይ የሚሞላዉን መጠይቅ በትክክል መሙላት
2. በትክክል የተጻፈ CV
3. የማመልከቻ ደብዳቤ (Cover letter)
4. ለስራዉ ይጠቅማሉ የምትሏቸዉን 5 ድረስ የሚጠጉ ምስክር ወረቀቶች ማስገባት

በምታመለክቱት ስራ እንዲሳካለችሁ ማድረግ ያለባችሁ ምክሮች ፡-
1ኛ. የስራ ልምድ በመጠይቁ ላይ ስትሞሉ በሰራችሁባቸዉ ቦታዎች ላይ ያስመዘገባችሁትን ዉጤት ላይ ማተኮር
2ኛ. የምታመለክቱት ስራ የሚፈልገዉን ክራይቴሪያ በተቻለ መጠን በደምብ ማተኮር

ስለ ድርጅቱ ጠለቅ ብለዉ ማወቅ ከፈለጉ ይሄንን ስለድርጅቱ  ይሄንን ሊንክ በመጫን ያግኙ።

ማስታወቂያዎቹ የሚገኙት በድርጅቱ ድረ ገጽ ሲሆን ይሄንን ሊንክ በመጫን ያገኟቸዋል።

በስራዎቹ ላይ ለመሳተፍ እና ለማመልከት በ ስራ ማመልከቻ ድረ ገጻቸዉ ላይ በመመዝገብ አካዉንት ማዉጣት ይኖርቦታል። የማመልከቻ አካዉንት ለመክፈት
1ኛ. ከስር ያለዉን ምስል ስትጫኑ የሚመጣዉ ድረ ገጽ ላይ መመዝገብ።

2ኛ. የሚፈልጉትን ሀገር ከስር በምስሉ ላይ እንደተመለከተዉ በመምረጥ በመመምረጥ ከሚመጡት ስራዎች የሚፈልጉት ላይ በመጫን ካሉበት ቦታ በኦንላይን ማመልከት ይችላሉ።

3ኛ. የሚፈልጉትን ስራ ከመረጡ በኋላ Apply online የሚለዉን ቁልፍ በመጫን ማመልከት ይችላሉ።

መልካም ሥራ።

Continue Reading
You may also like...

MD, Lecturer, UX & UI Developer, Consultant SMM, and Blogger.

More in ጉርሻ

To Top